Skip Navigation Links    
     





 

 
በጎንደር ከተማ የሚገኙ የመስህብ ስፍራዎችን ከጎበኙ ቱሪስቶች ከ28 ሚሊዬን ብር በላይ ገቢ ተገኘ

Monday, February 08, 2010

 
     
   

 አዲስ አበባ የካቲት 1/2002(ሬዲዮ ፋና) ገቢው  የተገኘው ባለፉት ሰባት ወራት  የመስህብ  ስፍራዎችን  ከጎበኙ  ከ56  ሺህ በላይ  የሃገር  ውስጥና  የውጭ  ሃገር  ቱሪስቶች  ነው።

 

የመስህብ  ስፍራዎቹን  ከጎበኙት  መካከል 18 ሺህ ያህሉ የውጪ  ሀገር ቱሪስቶች  መሆናቸውንም በከተማው ባህል ቱሪዝም  ሰራተኛና  ማህበራዊ  ጉዳይ  መምሪያ  የቱሪዝም  ልማትና  ፕሮሞሽን ባለሙያ አቶ ፀጋዮ ገብረ  መስቀል   አብራርተዋል፡፡

 

ቱሪስቶቹ  ከጎበኟቸው  መካከል  የፋሲል  አብያተ መንግስታት፣የፋሲለደስ መዋኛ፣የቁስቋም ቤተ መንግስትና  የደብረ  ብርሃን ስላሴ ቤተ ክርስቲያን  እንደሚገኙበት  አመልክተዋል።

 

ገቢው  ይገኛል ተብሎ  ከታቀደው  በ5 ሚሊዬን ብር  ያህል ፣የጎብኝዎች  ቁጥር  ደግሞ  በ9  ሺህ  ብልጫ  ያለው  መሆኑን  ባለሙያው ጠቁመዋል።

 

በዚህ  ዓመት  በከተማው  የሚገኙ  የመስህብ  ስፍራዎችን  80  ሺህ  የሚጠጉ  የሃገር  ውስጥና የውጭ  ሃገር ቱሪስቶች ይጎበኛሉ ተብሎ  የሚጠበቅ መሆኑን አስርድተዋል፡፡

 

ከዘርፉ  ከ40   ሚሊዮን ብር በላይ  ገቢ  ለመሰብሰብ  ታቅዶ  እንቅስቃሴ  እየተደረገ  መሆኑንም   አቶ ፀጋዮ  ጨምረው  ተናግረዋል።