Skip Navigation Links    
     





 

 
በኢትዮጵያ መንግስትና በተባበሩት የምዕራብ ሶማሌ ነፃ አውጪ ግንባር መካከል የሰላም ስምምነት ተፈረመ

Thursday, July 29, 2010

 
     
   

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22 2002 (ሬዲዮ ፋና) በኢትዮጵያ መንግስትና በተባበሩት የምዕራብ ሶማሌ ነፃ አውጪ ግንባር በቀድሞ መጠሪያው አል ኢትሃድ መካከል የሰላም ስምምነት ተፈረመ።

 

                ስምምነቱን በኢትዮጵያ መንግስት በኩል የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያምና የተባበሩት የምእራብ ሶማሌ ነጻነት ግንባር ሊቀ መንበር ሸክ ኢብራሂም መሃመድ ፈርመዋል።

 

  ለሰላም ስምምነቱ ኢትዮጵያ ጥረት ስታደርግ መቆየቷን የተናገሩት ሚኒስትሩ ዶክተር ሽፈራው የሰላም ስምምነቱ  ለሶማሌ ክልልም ሆነ ለመላው የሃገራችን ህዝብ ጠቀሜታው የጎላ ነው ብለዋል።

 

   የተባበሩት ምእራብ ሶማሊያ ነጻነት ግንባር  ለሰላም ያሳየውን ቁርጠኝነትና ሃላፊነት ያደነቁት ዶክተር ሽፈራው ጸረ- ሰላም  ዓላማ  ይዘው  የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች ስምምነቱን በአርአያነት ሊወስዱት እንደሚገባም ተናግረዋል።

 

    የግንባሩ ሊቀ መንበር ሸክ ኢብራሂም መሃመድ በበኩላቸው ከጦርነት ይልቅ ሰላምን ምርጫቸው አድርገው  ስምምነቱን በመፈረማቸው ደስተኞች መሆናቸውን ጠቅሰው በሶማሌ ክልል እየተካሄደ ባለው ልማትም ከህዝቡ ጎን በመቆም  የራሳቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።

 

 
     
 
Other Stories

የምንዛሬ ተመን ማስተካከያው የተጀመረውን ዕድገት ለማስቀጠል ይረዳል ተባለ

የመረጃ ነጻነት ህግ አገራዊ ተፈጻሚነት እንዲኖረው ነጻ በሆነ መልኩ መፈጸም ይኖርበታል ተባለ

የውጭ ምንዛሪ ተመን ለውጡ የወጪ ንግድን ለማጠናከር ይረዳል --- የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት

አዲሱ የከፍተኛ ትምህርት መመሪያ ጥራትን ለማረጋገጥ የተቀረፀ መሆኑ ተጠቆመ

የታዳሽ ኃይል ዘርፍ ጥቅምን ለማረጋገጥ ፕሮጀክት ተዘጋጀ

ኮርፖሬሽኑ ሰሞኑን "አደገኛ የሞባይል ፍሪኩዌንሲ በጤና ላይ አደጋ ያደርሳል" ተብሎ የሚናፈሰው ወሬ መሰረተ ቢስ መሆኑን አስታወቀ

ለህጻናት የፓርላማ አባላት ስልጠና እየተሰጠ ነው

አምስት ዩኒቨርሲቲዎች፣ የምርምር ተቋማትና ኢንዱስትሪዎች የኢትዮጵያ የላቦራቶሪ ማህበርን ሊመሰርቱ ነው

ያልተመዘገቡ የበጎ አድራጎት ደርጅቶችና ማህበራት የያዟቸውን ንብረቶች እንዲያስረክቡ ሊደረግ ነው

በፌዴራሊዝም ስርዓት ዙሪያ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እየተሰራ ነው