Skip Navigation Links    
     





 

 
ባለሃብቶች በሻይ ቅጠል ልማት መሰማራት የሚችሉበት አመቺ ሁኔታ መኖሩ ተጠቆመ

Thursday, July 29, 2010

 
     
   

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22 2002 (ሬዲዮ ፋና) ኢትዮጵያ ባለሃብቶች በሻይ ቅጠል ልማት ለመሰማራት የሚችሉበት ከስድስት ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬትና አመቺ ሁኔታ እንዳላት የግብርናና ገጠር ልማት ሚኒስቴር አመለከተ፡፡

 

ለልማቱ የሚሆነው መሬት በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በጋምቤላና በአማራ ክልሎች በስፋት እንደሚገኝ የገለጸው ሚኒስቴሩ የአገሪቱ የደጋ ሻይ ጣዕም በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተፈላጊነትና ተቀባይነት እያገኘ መምጣቱን  አመልክቷል፡፡

 

               በአገራችን በአሁኑ ጊዜ በሻይ ቅጠል የለማው መሬት 2 ሺህ 700 ሄክታር መሬት ብቻ መሆኑንና ከዚህም የሚገኘው ዓመታዊ ምርት ከሰባት ሺህ ቶን እንደማይበልጥ ተገልጿል።

 

               እንደ ኢዜአ ዘገባ ይህንን መሠረት በማድረግም ሚኒስቴሩ ባዘጋጀው የሻይ ቅጠል ልማት ቢዝነስ ዕቅድ ባለሃብቶች ሰባት ሺህ ሄክታር በሚደርስ መሬት ላይ ልማቱን እያካሄዱ ናቸው።

 

 
     
 
Other Stories

የምንዛሬ ተመን ማስተካከያው የተጀመረውን ዕድገት ለማስቀጠል ይረዳል ተባለ

የመረጃ ነጻነት ህግ አገራዊ ተፈጻሚነት እንዲኖረው ነጻ በሆነ መልኩ መፈጸም ይኖርበታል ተባለ

የውጭ ምንዛሪ ተመን ለውጡ የወጪ ንግድን ለማጠናከር ይረዳል --- የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት

አዲሱ የከፍተኛ ትምህርት መመሪያ ጥራትን ለማረጋገጥ የተቀረፀ መሆኑ ተጠቆመ

የታዳሽ ኃይል ዘርፍ ጥቅምን ለማረጋገጥ ፕሮጀክት ተዘጋጀ

ኮርፖሬሽኑ ሰሞኑን "አደገኛ የሞባይል ፍሪኩዌንሲ በጤና ላይ አደጋ ያደርሳል" ተብሎ የሚናፈሰው ወሬ መሰረተ ቢስ መሆኑን አስታወቀ

ለህጻናት የፓርላማ አባላት ስልጠና እየተሰጠ ነው

አምስት ዩኒቨርሲቲዎች፣ የምርምር ተቋማትና ኢንዱስትሪዎች የኢትዮጵያ የላቦራቶሪ ማህበርን ሊመሰርቱ ነው

ያልተመዘገቡ የበጎ አድራጎት ደርጅቶችና ማህበራት የያዟቸውን ንብረቶች እንዲያስረክቡ ሊደረግ ነው

በፌዴራሊዝም ስርዓት ዙሪያ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እየተሰራ ነው