Skip Navigation Links    
     





 

 
የአለም የኤች አይ ቪ ኤድስ የጋራ ፕሮግራም ኢትዮጵያ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ያደረገችውን እንቅስቃሴ አደነቀ

Wednesday, July 28, 2010

 
     
   

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21 2002 (ሬዲዮ ፋና) የአለም የኤች አይ ቪ ኤድስ የጋራ ፕሮግራም ኢትዮጽያ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ያደረገችውን እንቅስቃሴ አደነቀ።

 

 

የአለም የኤች አይ ቪ ኤድስ የጋራ ፕሮግራም ዋና ሃላፊ ሚስተር ሚቼል ሲዲቤ በኢትዮጽያ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸው።

 

የጉብኝቱ አላማም ኢትዮጽያ ከሌሎች ሃገራት ጋር የገባቻቸውን ውሎች ተግባራዊ ማድረጓን ለማረጋገጥ እና የምእተ አመቱን ግብ ለማሳካት መደረግ ባለበት ጉዳይ ላይ ለመምከር ነው።

 

የኢትዮጽያ ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ዕህፈት ቤት ያከናወናቸውን ተግባራት ሪፖርት ያደመጡት ሃላፊው ሃገሪቱ ስርጭቱን ለመግታት በተለይም ህብረተሰብ ተኮር በሆነ የመከላከል ተግባር ላይ ያደረገችውን እንቅስቃሴ አድንቀዋል ።

 

በቀጣይም ዕህፈት ቤታቸው  በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆኑንም አረጋግጠዋል።

 

ዋና ሃላፊው በቀጣይም የጳውሎስን ሆስፒታል ጨምሮ ሌሎች መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችንም ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

 
     
 
Other Stories

የምንዛሬ ተመን ማስተካከያው የተጀመረውን ዕድገት ለማስቀጠል ይረዳል ተባለ

የመረጃ ነጻነት ህግ አገራዊ ተፈጻሚነት እንዲኖረው ነጻ በሆነ መልኩ መፈጸም ይኖርበታል ተባለ

የውጭ ምንዛሪ ተመን ለውጡ የወጪ ንግድን ለማጠናከር ይረዳል --- የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት

አዲሱ የከፍተኛ ትምህርት መመሪያ ጥራትን ለማረጋገጥ የተቀረፀ መሆኑ ተጠቆመ

የታዳሽ ኃይል ዘርፍ ጥቅምን ለማረጋገጥ ፕሮጀክት ተዘጋጀ

ኮርፖሬሽኑ ሰሞኑን "አደገኛ የሞባይል ፍሪኩዌንሲ በጤና ላይ አደጋ ያደርሳል" ተብሎ የሚናፈሰው ወሬ መሰረተ ቢስ መሆኑን አስታወቀ

ለህጻናት የፓርላማ አባላት ስልጠና እየተሰጠ ነው

አምስት ዩኒቨርሲቲዎች፣ የምርምር ተቋማትና ኢንዱስትሪዎች የኢትዮጵያ የላቦራቶሪ ማህበርን ሊመሰርቱ ነው

ያልተመዘገቡ የበጎ አድራጎት ደርጅቶችና ማህበራት የያዟቸውን ንብረቶች እንዲያስረክቡ ሊደረግ ነው

በፌዴራሊዝም ስርዓት ዙሪያ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እየተሰራ ነው