Skip Navigation Links    
     





 

 
17 ቢሊየን ብር የሚያወጡ የመንገድ ልማት ፕሮጀክቶች ለሀገር ውስጥ ተቋራጮች መሰጠታቸውን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ገለጸ

Wednesday, July 28, 2010

 
     
   

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21 2002 ባለፉት 12 አመታት ውስጥ 17 ቢሊየን ብር የሚያወጡ የመንገድ ልማት ፕሮጀክቶች

ለሀገር  ተቋራጮች መሰጠታቸውን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ገለጸ።

          የሃገር በቀል የስራ ተቋራጮች ከ1989 እስከ 1994 ባለው የመጀመሪያው ዙር የመንገድ ልማት ዘርፍ በገጠር መንገዶች ላይ ብቻ የተወሰነና በቁጥርም አነስተኛ ተሳትፎ ነበራቸው።

 

    በ2ኛውና በ3ኛው የመንገድ  ልማት ዘርፍ ግን የሃገር በቀል ተቋራጮች ተሳትፎ በእጅጉ ጨምሯል። በኮንክሪት አስፋልት በሚሰሩ የመንገድ ፕሮጀክቶች ላይም በስፋት እስከመሳተፍ መድረሳቸውን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሳምሶን ወንድሙ ገልጸዋል።

 

 በአቅም ግንባታና በተለያዩ ዘርፎች አቅማቸው እንዲጎለብት ባለስልጣኑ ለሃገር ውስጥ ተቋራጮች የተለያዩ ድጋፎችን እንደሚሰጥ ጠቁመው ያም ሆኖ በአንዳንድ የሃገር ውስጥ ተቋራጮች የስራ ጥራት መጓደልና የመዘግየት ችግር እንደሚስተዋል ተናግረዋል።

 

  ባለፉት 12 ዓመታት የመንገድ ልማት ፕሮግራም አፈፃፀም 641 የመንገድ ፕሮጀክቶች ለጨረታ የወጡ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 404 የመንገድ ፕሮጀክቶች በሃገር በቀል የስራ ተቋራጮችና አማካሪዎች የተከናወኑ መሆናቸው ተመልክቷል።

 

              በእነዚህ አመታት ውስጥ 45 ቢሊየን ብር ለመንገድ ፕሮጀክቶቹ ወጪ የተደረገ ሲሆን 17 ቢሊየን ብሩ የሃገር ውስጥ ተቋራጮች የተሳተፉበት ነው።

 

          ይህም ሆኖ የሃገር ውስጥ ተቋራጮች ከውጭ ሃገር ከሚመጡ ተቋራጮች አንጻር አቅማቸው ዝቅተኛ በመሆኑ ከፍተኛ የፋይናንስ ወጪ በሚጠይቁና ረጃጅም ኪሎ ሜትሮችን በሚሸፍኑ የመንገድ ግንባታዎች ላይ ተሳታፊ መሆን እንዳልቻሉ ጠቅሰው የሃገር ውስጥ ተቋራጮችም አቅማቸውን በማጎልበት ችግራቸውን በዘላቂነት ሊፈቱ ይገባል ብለዋል።

 

የሚስተዋለው የአቅም ችግር በዋናነት መፈታት ያለበት በራሳቸው በድርጅቶቹ መሆኑን አንዳንድ

የተቋራጭ ድርጅቶች ጠቁመው መንግስት ለዘርፉ በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት የተለያዩ ማሽነሪዎች ከውጭ ከቀረጥ ነፃ በሆነ ሁኔታ እንዲገቡ በመፍቀዱ በዚህ ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል።    

 

 

          አያይዘውም ይህ የመንግስት ከፍተኛ ድጋፍ የሃገር ውስጥ ተቋራጮች ተሳትፎ እንዲያድግ በማድረጉ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳለውና በቀጣይም መንግስት ይህንኑ አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አስረድተዋል።

 

           በቀጣዮቹ አመታት የተሻለና ጥራት ያለው መንገድ በመስራት ተወዳዳሪነታቸውን ከፍ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን የባልደረባችን የመሰረት ገዛኸኝ ዘገባ ያመለክታል።

 

 
     
 
Other Stories

የምንዛሬ ተመን ማስተካከያው የተጀመረውን ዕድገት ለማስቀጠል ይረዳል ተባለ

የመረጃ ነጻነት ህግ አገራዊ ተፈጻሚነት እንዲኖረው ነጻ በሆነ መልኩ መፈጸም ይኖርበታል ተባለ

የውጭ ምንዛሪ ተመን ለውጡ የወጪ ንግድን ለማጠናከር ይረዳል --- የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት

አዲሱ የከፍተኛ ትምህርት መመሪያ ጥራትን ለማረጋገጥ የተቀረፀ መሆኑ ተጠቆመ

የታዳሽ ኃይል ዘርፍ ጥቅምን ለማረጋገጥ ፕሮጀክት ተዘጋጀ

ኮርፖሬሽኑ ሰሞኑን "አደገኛ የሞባይል ፍሪኩዌንሲ በጤና ላይ አደጋ ያደርሳል" ተብሎ የሚናፈሰው ወሬ መሰረተ ቢስ መሆኑን አስታወቀ

ለህጻናት የፓርላማ አባላት ስልጠና እየተሰጠ ነው

አምስት ዩኒቨርሲቲዎች፣ የምርምር ተቋማትና ኢንዱስትሪዎች የኢትዮጵያ የላቦራቶሪ ማህበርን ሊመሰርቱ ነው

ያልተመዘገቡ የበጎ አድራጎት ደርጅቶችና ማህበራት የያዟቸውን ንብረቶች እንዲያስረክቡ ሊደረግ ነው

በፌዴራሊዝም ስርዓት ዙሪያ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እየተሰራ ነው