አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21 2002 (ሬዲዮ ፋና) በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ወደ ውጭ ከተላከ የቁም እንስሳትና የስጋ ምርት ከ124 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ።
የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አማከለ ይማም ለዋልታ እንደተናገሩት ገቢው የተገኘው 317 ሺህ የቁም እንስሳትንና 34 ሺ ቶን የስጋ ምርት ለገበያ በማቅረብ ነው።
ገቢውም ይገኛል ተብሎ ከነበረው እቅድ የ7 ነጥብ 3 ሚሊየን ዶላር ብልጫ አለው ።
በቀጣይም ምርቶቹ የሚላኩባቸውን ሃገራት ቁጥር ከፍ በማድረግ ገቢውን ይበልጥ ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።