Skip Navigation Links    
     





 

 
እስካሁን 60 ሺ ተማሪዎች ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች ተመርቀዋል

Tuesday, July 27, 2010

 
     
   

ዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20 2002 (ሬዲዮ ፋና)  በሀገሪቱ የሚገኙ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠኗቸው 59 ሺ 993 ተማሪዎች በቅርቡ ተመርቀዋል። በአገራችን እየተመዘገበ ለሚገኘው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አስተዋጽኦ የላቀ መሆኑን  የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች በምረቃው ላይ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በአካል መገኘት ባይችሉም በቪዲዮ ባስተላለፉት መልዕክት ተመራቂዎቹ ቀጣይ የስራ ዘመናቸው የተሳካ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን እንዲሁም ዩኒቨርሲቲው ለክብር ዶክትሬት ላበቃችው ግለሰቦችም ያላቸውን ክብር ገልጸዋል። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 10 ሺ483፣ የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ 8ሺ 786፣ የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ 4ሺ 912፣ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ 4 ሺ 266፣ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ 3ሺ400፣ አዳማ ዩኒቨርሲቲ  3ሺ፣ የመዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ 1ሺ 223 ፣  የወለጋ ዩኒቨርሲቲ 1 ሺ 600፣  የጅማ ዩኒቨርሲቲ 1ሺ850፣ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከ1ሺ 300 በላይ እንዲሁም  የሰመራ ዩኒቨርሲቲ 815 ተማሪዎችን አስመርቀዋል።

"እናንተ ተመራቂዎች ላለፉት ዓመታት በተለያዩ መስኮች ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ  ለመመረቅ በቅታችኋል ፤ አሁን የሀገር ዕድገትን ለማጠናከርና ገፅታዋን ለመቀየር ብዙ መስራት ይጠበቅባችኋል" የሚለው መራቂዎቹ ካሰተላለፏቸው መልዕክቶች የሚጠቀስ ነው ።ተመራቂዎቹ ከፈጸሙት ቃለ መሃላ መካከልም " ሃገራችን ኢትዮጵያን ከድህነትና ኋላ ቀርነት ለማላቀቅ፣ልማት ዲሞክራሲና መልካም አስተዳደር ለማስፈን በሚደረጉት ጥረቶች የድርሻዬን ለማበርከት ህዝብና መነግስት የጣለብኝን ኃላፊነት ለመወጣት ቃል እገባለሁ" የሚለው ይገኝበታል።

 ዩኒቨርሲቲዎቹ በመንግስት በተመደበላቸው በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ የማስፋፊያ ግንባታ እያካሄዱ መሆኑንም የየዩኒቨርሲቲዎቹ ፕሬዝዳንቶች በምረቃው ወቅት ተናግረዋል።  
               በዚህም መሰረት የአዲስ አባበ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ የትምህርት ዘርፍ ያሰለጠናቸውን 10 ሺ 483 ተማሪዎችን ባለፈው ቅዳሜ ሲያስመርቅ ከዚህም ውስጥ 2ሺ 280 በሁለተኛ ዲግሪ እና 15 በዶክትሬት ዲግሪ አስመርቋል። ዩኒቨርሲቲው በአምስት አመት ውስጥ 5ሺ የዶክትሬት ተማሪዎችን ለማስመረቅ እቅድ መያዙን በምረቃው ስነ ስርአት ላይ ተመልክቷል። 
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በአካል መገኘት ባይችሉም በቪዲዮ ባስተላለፉት መልዕክት ተመራቂዎቹ ቀጣይ የስራ ዘመናቸው የተሳካ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን እንዲሁም ዩኒቨርሲቲው ለክብር ዶክትሬት ላበቃችው ግለሰቦችም ያላቸውን ክብር ገልጸዋል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት አንድሪያስ እሸቴ "ካካበታችሁት ክህሎትና አቅም በተጓዳኝ ተወዳዳሪነትና ቁርጠኝነትን መላበስ ይኖርባችኋል" በማለት መልዕክታችውን አስተላልፈዋል።
 የሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ  4ሺ912፣ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ 3ሺ400፣ አዳማ ዩኒቨርሲቲ  3ሺ፣ እንዲሁም የመዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ 1ሺ223  ተማሪዎችን አስመርቀዋል። የመዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ካስመረቃቸው ተማሪዎች ውስጥ 1ሺ815ቱ ሴቶች ናቸው።
 የጅማ ዩኒቨርሲቲ 1ሺ850 ተማሪዎችን ሲያስመርቅ ከዚህ ውስጥ 42ቱ በሁለተኛ ዲግሪ የተመረቁ ናቸው። በተጨማሪም የአምቦ ዩኒቨርሲቲ 1664፣ የደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ 1560 እና የጅጅጋ ዩኒቨርሲቲ 1073 ተማሪዎችን አስመርቀዋል። የጅጅጋ ዩኒቨርሲቲ በስምንት ፋካሊቲዎች ሰላሳ ሁለት ዲፓርትመንቶችን ከፍቶ 5ሺ400 ተማሪዎችን እያስተማረ እንደሚገኝ በምረቃው እለት ተገልጿል። 
የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ  በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 8ሺ786 ተማሪዎችን በአራት ዙር አስመርቋል።  270ዎቹ በሁለተኛ ዲግሪ ነው።
 ዩኒቨርሲቲው ባለፉት አመታት በቴክኖሎጅና በምህንድስና የሙያ መስኮች ለኢኮኖሚያዊ እድገት ጠቃሚ ተግባር እያከናወነ እንደሚገኝ የዩነቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር የሺ መብራት ጠቁመዋል።
እንዲሁም የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ በ49 የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 4 ሺ266 ተማሪዎች  አስመርቋል። ከእነዚህ መካከልም 182ቱ በሁለተኛ ዲግሪ መርሃ ግብር የሰለጠኑ ናቸው። ዩኒቨርሲቲው ለትምህርት ጥራት መጠበቅና ለምርምር ስራ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ምትኩ ሀይለ ተናግረዋል።
  በ49 የመጀመሪያና በ27 ሁለተኛ የትምህርት ዘርፎች ከ21 ሺ የሚበልጡ ተማሪዎችን ተቀብሎ በመደበኛ ፣ በተከታታይና በክረምት የስልጠና መርሃ ግብር በማስተማር ላይ የሚገኘው የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ በሚቀጥለው ዓመት በአፈር ሳይንስ የዶክትሬት ሰልጠናና በስድስት ፕሮግራሞች የሁለተኛ ዲግሪ ስልጠና ለመጀመር መዘጋጀቱ ተጠቁሟል።
በተያያዘ ዜና የሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ በተለያየ የትምህርት ዘርፍ ያሰለጠናቸውን 576 ተማሪዎች ሲያስመርቅ 138ቱን በመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም ቀሪዎቹን 438 ደግሞ በሁለተኛ ዲግሪ አስመርቋል። የጋምቤላ መምህራን ማሰልጠኛ ተቋም 183 አድማስ ኮሌጅ ደግሞ 90 ተማሪዎችን በዲፕሎም  መርህ ግብር አስመርቀዋል። አድማስ ኮሌጅ ካስመረቃቸው መካከልም 60% የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸው ተመልክቷል።
 በተመሳሳይ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለሁለተኛ ጊዜ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ከ1ሺ 300 በላይ ተማሪዎችን በመጀመሪያ ዲግሪ ሲያስመርቅ የወሎ ዩኒቨርሲቲ 913፣ የሰመራ ዩኒቨርሲቲ 815 እንዲሁም የወለጋ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ፤ በማታና በክረምት ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 600 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡ የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ካስመረቃቸው መካከል 300 ያህሉ ሴቶች መሆናቸው ተመልክቷል፡፡
የደብረ ብርሀን መምህራን ትምህርትና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ በልዩ ልዩ ሙያ ያሰለጠናቸውን 1ሺህ 113 ተማሪዎች በዲኘሎማ አስመርቋል፡፡ በመደበኛውና በማታው ክፍለ ጊዜ አሰልጥኖ ካስመረቃቸው ተማሪዎች መካከል 995ቱ በመምህርነት ቀሪዎቹ ደግሞ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የሰለጠኑ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው፡፡
 የኮተቤ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ከ1 ሺህ 700 በላይ እጩ መምህራንን በዲፕሎማና በምስክር ወረቀት አስመርቋል፡፡ የደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በበኩሉ በመምህርነት ሙያ ያሰለጠናቸውን 1ሺህ 554 መምህራንን በዲፕሎማ አስመርቋል።
 የባህርዳር ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጅ ከደረጃ አንድ እስከ ደረጃ አራት ያሰለጠናቸውን 2211 ተማሪዎችን ሲያስመርቅ የደብረ ታቦር ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ 1085፣ የደብረ ማርቆስ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ከ1000 በላይ ተማሪዎችን አስመርቀዋል።  
በተጨማሪም የግልገል በለስ መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ በመደበኛና በማታው መርሀ ግብር ያሰለጠናቸውን ከ600 በላይ እና የሀረር መምሀራን ትምህርት ኮሌጅ 475 እጩ መምህራንን ሲያስመርቁ የጅጅጋ ቴክኒክ ሙያና የውሀ ቴክኖሎጅ 1600 ተማሪዎችን አስመርቋል። ኮሌጁ ባለፉት ዘጠኝ አመታት ከ5 ሺ በላይ ተማሪዎችን ማስመረቁ ተመልክቷል።

 
     
 
Other Stories

የምንዛሬ ተመን ማስተካከያው የተጀመረውን ዕድገት ለማስቀጠል ይረዳል ተባለ

የመረጃ ነጻነት ህግ አገራዊ ተፈጻሚነት እንዲኖረው ነጻ በሆነ መልኩ መፈጸም ይኖርበታል ተባለ

የውጭ ምንዛሪ ተመን ለውጡ የወጪ ንግድን ለማጠናከር ይረዳል --- የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት

አዲሱ የከፍተኛ ትምህርት መመሪያ ጥራትን ለማረጋገጥ የተቀረፀ መሆኑ ተጠቆመ

የታዳሽ ኃይል ዘርፍ ጥቅምን ለማረጋገጥ ፕሮጀክት ተዘጋጀ

ኮርፖሬሽኑ ሰሞኑን "አደገኛ የሞባይል ፍሪኩዌንሲ በጤና ላይ አደጋ ያደርሳል" ተብሎ የሚናፈሰው ወሬ መሰረተ ቢስ መሆኑን አስታወቀ

ለህጻናት የፓርላማ አባላት ስልጠና እየተሰጠ ነው

አምስት ዩኒቨርሲቲዎች፣ የምርምር ተቋማትና ኢንዱስትሪዎች የኢትዮጵያ የላቦራቶሪ ማህበርን ሊመሰርቱ ነው

ያልተመዘገቡ የበጎ አድራጎት ደርጅቶችና ማህበራት የያዟቸውን ንብረቶች እንዲያስረክቡ ሊደረግ ነው

በፌዴራሊዝም ስርዓት ዙሪያ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እየተሰራ ነው